በሁለት ዙር ለሚደረግ ሥልጠና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመንግሥት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራሞች ዙርያ ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ሥልጠናውን የማይሳተፉ ተማሪዎች ለቀጣዩ ዓመት ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት መመዝገብ እንደማይችሉም ታውቋል፡፡
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተመደቡበት ጣቢያ ለ15 ቀን ያህል በሁለት ዙር የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና የፕሮግራም ሥልጠና ከመስጠት ባሻገር በመማር ማስተማር ሒደቱ ስለሚከሰቱ ተግዳሮቶች፣ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎችና የመልካም ዜጋ ባህሪያት ላይ ጥልቅ ውይይቶች እንደሚደረጉ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በየዓመቱ መጀመርያ ላይ ካለፈው ዓመት የመማር ማስተማር ሒደት ግምገማ ማድረግ የተለመደ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ደሳለኝ፣ የትምህርት ጊዜን ላለመሻማትና በአዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ የተነሳ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ጊዜ የተለያየ በመሆኑ በክረምቱ ወቅት ሥልጠናውን ለመስጠት እንደመረጡም አመልክተዋል፡፡ በሥልጠናው ላይ ተካፋይ የሆኑ ተማሪዎች ሥልጠናው አስገዳጅ በመሆኑ ነፃነታቸውን የሚጋፋ መሆኑን ለሪፖርተር መግለጻቸውን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ፣ ሥልጠናው የትምህርታቸው አንድ አካል በመሆኑ መሠልጠን የማይፈልጉበት ምክንያት እንደማይታያቸው ገልጸዋል፡፡ ሥልጠና ለማይካፈሉ መመዝገብ የተከለከለ ስለመሆኑም የተወሰነው በትምህርት ሚኒስቴር እንደሆነም አረጋግጠዋል፡፡ በሥልጠናው ላይ ከ250,000 በላይ የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ከ116,000 በላይ አዳዲስ ተማሪዎች እንደሚሳተፉ የተጠቆመ ሲሆን፣ ሥልጠናው በትምህርት ሚኒስቴርና በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በጋራ መዘጋጅቱም ተገልጿል፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሥልጠናው በሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች፣ በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና በኢትዮጵያ ህዳሴ ላይ እንደሚመክር የዘገቡ ሲሆን፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሥልጠናው በመጪው ዓመት ከሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዓመፅ እንዳይቀሰቅሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ ግን በቅርብ ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ምንም ዓይነት ኮሽታ አለመሰማቱን ጠቁመው፣ ሥልጠናው በአጠቃላዩ የመማር ማስተማር ሒደት ላይ ከመምከርና የመንግሥት አሠራሮችን ከማስተዋወቅ ባሻገር ከምርጫ 2007 ጋር የሚያገናኘው ምንም እንደሌለ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ምንጭ፦ ሪፖተር ጋዜጣ _____________________________________________________ We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers. የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፊቼ በኣል በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ መመዝገቡ ተሰማ፤ በኣሉ ከትናንትና ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ኣለም በመከበር ላይ ነው7/23/2014 የፊቼን በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ከጫፍ መደረሱን ድረሳቸውን የሲዳማ ዞን የባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ገለፀ።
የመምሪያው ሀላፊ ካላ ወርቅነህ ፍላቴን ጠቅሶ ፋና እንደዘጋበው፥ የፊቼን በኣል በዩ ኔስኮ በማስመዝገቡ እንቅስቃሴ የመሪነቱን ሚና በመጫዎት ላይ ያለው የሲዳማ ዞን በአሉ በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ መመዝገቡን የምገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው ኣስታውቋል። ኣገሪቱን የማይዳሰሱ ቅርሶች በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በተደረገው እንቅስቃሴ እስከኣሁን የመስቀልን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን፤ ከመሰቀል በኣል ውጭ የፊቼን እና ሌሎች የማይዳሰሱ የኣገሪቱን ብርቅዬ ባህላዊ ቅርሶች በዩኔስኮ የማስመዝገቡ ህደት ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል። የፊቼ በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት መመዝገብ በኣሉን ለማሳደግ ብሎም ለመንከባከብ ከማስቻሉ በላይ የሲዳማን ህዝብ ባህላዊ ቱፊቶችን ለኣለም ህዝብ ለማስተዋወቅ ያስችላል። በኣሉ ከትናንትና ጀምሮ በመላዋ ሲዳማ በተለይ በሲዳማ መዲና በሃዋሳ ከተማ በታላቅ ድምቀት በተለያይ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ሲሆን፤ጠዋት ላይ የአርድና የትንበያ ስነስርአት በብሄረሰቡ አባቶች ተከናውኗል። በትንበያው ዘመኑ የሰላም የፍቅርና ወጣቱ ለስራ የሚነሳሳበት ዘመን ይሆናል ብለዋል። በዛሬው እለት የጨንበላላ በአል በመከበር ላይ ነው። በተያያዘ ዜና የፊቼ በኣል ከሲዳማ ውጭ በኣሜሪካ፤ በኣውሮፓ እና በደቡብ ኣፍሪካ በሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ ኣማካይነት በኣለም ኣቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ነው። የወራንቻ ኔትወርክ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤ በተለያዩ ኣገራት የምኖሩ የሲዳማ ኮሚኒት ኣባላት የፊቼን በኣል በግል እና በቡድን በመሆን የሲዳማን ባህላዊ ኣልባሳትን በመልበስ በማክበር ላይ ናቸው። ሲዳማ በኢትዮጵያ የሰነ ጽሁፍ ታርክ ኣንቱ የተባሉ ጸሃፊትን ኣፍርታለች። በተለይ ኣንጋፋዋ የሲዳማ ከተማ የሆነችው ይርጋዓለም/ ዳሌ በርካታ ደራሲያን እና ጸሃፍት የፈለቁባት ከተማ ናት።
ይርጋዓለም ለስነ ጽሁፍ የሚመች ድባብ ኣላት። ነዋሪዎቹዋም ይህንን ደባብ ተጠቅመው የጥበብ ስራዎቻቸውን ለሰነ ጥበብ ኣፍቃሪያን ማድረሳቸውን ተያይዘውታል። ምንም እንኳን በሲዳማ ቋንቋ ይህ ነው የምባል የጎላ ስራ ከይርጋዓለም ባይወጣም በኣማርኛ ቋንቋ ግን ኣያሌ ስራዎች ለንባብ በቅተዋል። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ይርጋዓለም_ዳሌ በኣገሪቱ ሰነ ጽሁፍ ያላትን ሚና ለመዘከር ኣንጋፋ ጸሃፊቷን ለኣንባቢያን ያስተዋውቃል፤ ለዛሬ ደራሲ እና ባለቅኔ ደበበ ሰይፉ እነሆ ብለናል፦ የደራሲው ሥራዎች 1. የብርሃን ፍቅር(ግጥምና ቅኔ) 2. ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ(ግጥምና ቅኔ) 3. ከባሕር የወጣ ዓሣ(ተውኔት) ስለደራሲው በጥቂቱ ደበበ ሰይፉ የአማርኛ ባለቅኔ ነበሩ። ሚያዚያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ደበበ ሰይፉ ዘርፈ ብዙ የጥበብ ሰው ነው፡፡ ገጣሚ፣ ሃያሲ፣ መምህር፣ ጸሐፊ-ተውኔት፣ የሥነ-ጽሑፍ ተመራማሪ… ነው፡፡ “የብርሃን ፍቅር” እና “ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ” የግጥም ሥብስቦቹ የተደጎሱባቸው መጻሕፍቱ ናቸው፡፡ ከዚህ ለጥቆ ያለው መረጃ /አቀናባሪ አሉላ ከ EthioCurrent Assimba –Voice Room/ አማካኝነት /የደበበ ሰይፉን 7ኛ ዓመት የሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ16,1999ዓ.ም የተቀናበረ ነው፡- “..ደበበ ሰይፉ ሐምሌ 5 ቀን 1942 ዓ.ም. በሲዳሞ፡ ይርጋለም ተወለደ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በይርጋለምና በአዲስ አበባ ኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤቶች ተማረ። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ከፍ ባለ ማዕረግ የመጅመሪያ ድግሪውን አገኘ። በእንግሊዘኛ ሥነ ጽሁፍ የማስተር ድግሪውን ተቀበለ። ከ1966 እስክ 1984 በረዳት ፕሮፌሰርነት አገለገለ። ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዜዳንት ሆኖ ሰራ። በቀድሞው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ያልታተሙ መፃህፍት ገምጋሚም ነበር። ከ1985 ዓ.ም. ጅምሮ ለሰባት ዓመታት ታሞ ማቀቀ። ሚያዝያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም. በተወለደ በሃምሳ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሚያዝያ 17 ቀን 1992 ዓ.ም. ንፋስ ስልክ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር በድኑ አረፈ። ከተማሪነቱ አንስቶ በርካታ ግጥሞች ጽፏል። «የብርሃን ፍቅር» የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥም መድበሉን በ1980 ዓ.ም. በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት አሳተመ። የብርሃን ፍቅር ሁለተኛ ክፍል የሆነውንና ፦ «ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ» የተሰኘውን መድበሉን ደግሞ በ1992 ዓ.ም. በሜጋ አሳታሚ ድርጅት ታተመ። በተውኔቱ ዘርፍ «የቲያትር ጥበብ ከፀሐፌ ተውኔቱ አንፃር» የሚለው መጽሐፉ፤ «ሳይቋጠር የተፈታ» እና «ከባህር የወጣ ዓሣ» የተሰኙት ቲያትሮቹ ቢጠቀሱ ይበቃል…ጥናታዊ ፅሁፎቹም በርካታ ናቸው። አታልቅስ አትበሉኝ አትሳቅስ በሉኝ ግዴለም ከልክሉኝ፤ የፊቴን ፀዳል አጠልሹት በከሰል፤ የግንባሬን ቆዳ ስፉት በመደዳ፤ ጨጓራ አስመስሉት። ግዴለም። አትጫወት በሉኝ ዘፈኔን ንጥቁኝ ግዴለም። ብቻ ፤ አታልቅስ አትበሉኝ አትጩህ አትበሉኝ ። ከሰባት ዓመት በፈት ደበበ ሰይፉ እንዳረፈ ሰሞን ስሙን፦ በጋዜጣ፤ በመጽሔት፤ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ሲነሳ ሲወሳ ከርሟል። እስከዛሬም ይታወሳል። ዛሬም ሰባተኛ የሙት ዓመቱን እንዘክረዋለን። ይህን የምናደርገው ፕሮፌሰር ስለሆነ ፤ ገጣሚ ስለሆነ ፤ አንደበተ ርቱዕ ስለሆነ ፤ ፀሐፊ ተውኔት ስለሆነ ፤ ጠቢብ ስልሆነ ብቻ አይደለም ። በዛሬው ዘመን ስለሱ ተወሳ - አልተወሳ ምንም ቁም ነገር የለውም። ሳንታሮ ታኒካዋ ፅፎት ጆርጅ ጊሽ ጀር የተረጎመውን፦ “What the dead man left behind” የሚለውን ግጥም አስታውሶ ትካዜ ባሟሸው ዝምታ ማለፍም ይቻል ነበር። ነገር ግን ጋሽ ደበበ ሁሉንም «ልዩ» ነገር እንደነበር የማያውቁት እንዲያውቁት ያስፈልጋል። ጋሽ ደበበ ሁሉንም «ልዩ» ነገር ነበር። ልዩ ፕሮፌሰር፤ ልዩ ባለቅኔና ገጣሚ፤ ልዩ ተናጋሪ (ኦራተር)፤ ልዩ ተፈላሳፊ፤ ልዩ ፀሕፊ ተውኔት፤ ልዩ ጠቢብ፤ ልይ ሩህሩህና ደግ፤ ልዩ «ቅዱስ» አማፂ፤ ልዩ ልዩ ነበር። ፍርሃት አዶከብሬ ፍርሃት አዶከብሬ አያ እናት አይምሬ የቁም መቃብሬ የቅዥት አገሬ። ከሥጋ ከነብሴ ከደሜ ቆንጥሬ ከአጥንቴ ሰንጥሬ፤ ምስህን ሰጥቼህ ላመልህ ገብሬ፤ ያው ነህ አንተገና ልጓምህ አይላላ። ትጋልበኛለህ በእሾህ በቆንጥር ላይ ጨለማ እንደ ግራር በቅሎበት በሚታይ አንዲት ዘሃ-ጮራ በማትደፍርበት እውነት - ፍቅር - ውበት በተቀበሩበት። ቅዱስ አማፂ ሆኖ ሳለ ከውስጡ አልነቀል ያለውን የፍርሃት ርዝራዥ በ«ፍርሃት አዶከብሬ» ውስጥ ያሳየናል። ካልፈራህ እንዴት ቅዱስ አማፂ ትሆናለህ? ትፈራለህ፤ ትደፍራለህ። ድፍረት በፍርሃትህ ልክ ነው። በፈራኸው መጠን ትደፍራለህ። የማትፈራ ከሆንክ፦ የማትደፍር ነህ። የማትደፍር ከሆንክ የማትደፈር ነህ፤ (ብዙ ጊዜ)። የማትፈራም የማትደፍርም ከሆንክ ደግሞ በድን ነህ። ቅዱስ አማፂነትህ የፍርሃትና የድፍረትህ ድምር ውጤት የሚሆንበት (አብላጫ) ጊዜ አለ። «ጋሼ ደበበ እንዴት ኮሚኒስት እንደሆነ» አንድ ስው ሲያወጋ፡- ያኔ ተማሪ ነበር አሉ። ስታዲየም ዙሪያ አንድ ምግብ ቤት ገባ። እርቦታል። ምግብ አዘዘ። የመብል አምሮት የሠራው ምራቅ በአፉ ግጥም እያለ ትንሽ «አፋዊ» ኩሬ ይሰራል። ያዘዘው ምግብ እስኪቀርብለት በመጠባበቅ ላይ እያለ አንድ ሰው በዝግታ ወደ ውስጥ ገባ። ቡትቶ ለብሷል፤ ዓይኖቹ በደረቀ ፊቱ ውስጥ ተቀርቅረዋል። እንደራበው ያስታውቃል። ተያዩ። የዓይን ግጭቱ ቁም ነገር ያዘለ ከባድ ሃሳብ ሰራ። ያ ሰው ሊናገር ከሚችለው በላይ ለጋሽ ደበበ መልዕክቱ ደረሰው፦ «እርቦኛል ፤ በልተህ ሲተርፍህ እንድትሰጠኝ» ነው ያሉት የሰውየው ዓይኖች። ጋሽ ደበበ ግን ከዚህ በላይ ገባው። አምሮት በሰራው ምራቅ ግጥም ያለ አፉ ክው አለ። የታዘዘው ምግብ እየመጣ ነበር። እፈቱ ተቀመጠ። መብሉን አየው ጋሽ ደበበ። ከመቀመጫው ተነሳ። አነሳው ምግቡን። ለሰውየው ሰጠው። መስጠት ጀምሮ መስጠቱ ከማብቃቱ በፊት በአንድ ጊዜ ሁለት ነገሮች ሆኑ…ከውጭ ግር ያሉ ቡትቶ የለበሰው ሰውዬ ጉስቁል አጃቢዎች መሻማት ጀመሩ። ይሄ አንዱ ነገር ነው። የምግብ ቤቱ ባለቤት ባለቡትቶውን ሰውዬ መቀጥቀጥ ጀመሩ፤ ይሄ ደግሞ ሌላው ነገር ነው። ምግቡ ተደፋ። ጐስቋላው ሰውዬ ደማ። ምግቡ፤ ደሙ፤ አሸዋው፤ አፈሩ፤ ጠጠሩ ሺህ ዓመት እዚያ ቦታ የቆመ ያህል ተሰማው። ተነቀሳቀሰ። ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ መራመድ ጀመረ። ከዚያን ቅፅበት ጅምሮ በኮሚኒዝም ተጠመቀ። ታላቁ መብረቅ ከሰባት ዓመት በፈት አመለጠ። ትናንት ከኛ ጋር ነበር፤ ዛሬ የለም። የጊዜ ጉዳይ ነው። በጊዜ ላይ ሲፈላሰፍ የቋጠራቸው ስንኞች ስለስብዕናው የሚሰጡት ስዕል አለ። ምንጭ: ውክፔዲያ Fair Trade, a certification system aimed at improving working conditions for some of the world’s poorest farmers, has recently come under fire.When David Pritchard runs out of Fair Trade coffee beans he’ll do what he always does: Order more.
The coffee roaster and co-owner of Birds & Beans café in Mimico, pays a premium for beans that come with the newly-controversial designation. “I think it does a lot of good,” he says, of the Fair Trade system. “It’s a work in progress — but a worthy one.” Fair Trade, a certification system aimed at improving working conditions for some of the world’s poorest farmers, has recently come under fire. U.K. researchers have cast doubt on whether paying more for coffee grown, harvested, picked and sold according to Fair Trade rules indeed promotes better wages and better working conditions for those toiling in the field. Researcher Christopher Cramer at SOAS University of London found that wage workers at their Fair Trade research sites in Ethiopia and Uganda are among the poorest and most destitute. By comparison, the Fairtrade, Employment and Poverty Reduction in Ethiopia and Uganda study (FTEPR) found that labourers at some smallholder independent farms and large-scale, commercial coffee operations alike, which are not associated with Fair Trade, are still “extremely poor” but on average are paid and treated better. Traditionally, the Fair Trade movement has aimed at improving the living and working conditions for family farmers by increasing the minimum cost of the coffee beans they produce. But the study discovered that many of those family farms also employ wage earners, Cramer says, often women and girls, who are often a given society’s most destitute. Researchers also discovered widespread child labour at many farms, including some associated with Fair Trade certifications. Last year, Fair Trade Canada anointed Toronto a Fair Trade city, making it the largest North American city to earn the designation at the time. More than 400 local stores and cafés sell items that bear the designation. Geoff Woodley of Detour Coffee, a Toronto roaster that sells to cafes across Canada, deliberately sidesteps the Fair Trade system, opting for Direct Trade coffee. This emerging movement develops direct relationships with small, independent farmers, rather than management teams of co-operative farms associated with Fair Trade. The emphasis, Woodley says, is on creating lasting “business relationships.” The Fair Trade model often means that several farmers blend their beans together, Woodley says, pooling a variety of different quality coffees. Going to the source not only puts money right into farmers’ hands, Woodley says, but rewards those who produce better beans. While Fair Trade coffee fetches $2 per pound for producers, Woodley says direct trade farmers often get $3 to $4 per pound of coffee. “We’re paying for quality above anything else,” he says. “It’s a sustainable model which creates a quality product.” Marika Escaravage, spokesperson for Fair Trade Canada, says the international organization was already investigating allegations of human rights violations, such as child labour, when Cramer’s study became news a few weeks ago. Escaravage says Fair Trade International is working to address the problem. But, she says, one study isn’t a reason to call into question 25 years of work, which has introduced democratic practices into coffee farming, increased the average price of coffee beans and helped improve the lives of many family farmers. Canada imports most of its coffee from Columbia, Peru, Honduras and Mexico, 2012 Fair Trade data shows, and buys very little from Ethiopia and Uganda. Still, it’s a complex problem without one easy answer, Escaravage says. “If you think that buying fair-trade coffee is going to solve all the problems in the world – sorry that’s not realistic,” she says. “But it is doing good. We’re constantly improving all the time.” For Pritchard, that’s the main point. “It’s raised awareness,” Pritchard says, of the Fair Trade movements. “To throw that all away now would be a huge mistake.” ምንጭ፦ thestar.com By Elise Dufief
International democracy promotion is challenged by the global retreat of democracy. The case of Ethiopia demonstrates how political space can be narrowed, a hegemonic regime strengthened, and election observer missions constricted in their capacity to influence outcomes. Election monitoring can deepen the contradictions between regime practices and democratic objectives. * Why does the Ethiopian government regularly organize elections and invite election observers only to reject their findings? How did the governing party come close to losing the 2005 election yet triumph in 2010 with 99.6% of the vote? Why do international actors such as the EU Observer Mission continue to participate in these processes where their credibility is likely to be tarnished? Such questions must be answered about the manipulation of democracy promotion instruments by a non-democratic regime. Continue reading →
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቱርክ አቻው ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ እንዲያደርግ መታቀዱን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ አስታወቁ።
አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በዛሬው እለት ስለቡድኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት። አሰልጣኙ መግለጫ ከሰጡባቸው ዋነኛ ሀሳቦች መካከል ፥ የመረጧቸው 38 ተጨዋቾች የዝግጅት ሂደት ምን ይመስላል የሚለው ይጠቀሳል። በተጨማሪም ዋነኛ አላማቸው በ2015 በሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ እንደሆነ በመግለፅ፥ አልጄሪያን ከመግጠማቸው በፊትም የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ቱርክ አቅንተው ለመጫወት እንደታሰበ አስረድተዋል። አብዛኛውን ተጨዋቾች በደንብ ስለሚያውቋቸው ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል ፀሀዬን እኔው እራሴ ምክትሎቼ አድርጌ መርጫቸዋለው ብለዋል በመግለጫቸው ላይ። ከ20 አመት በታች የሚገኙ ተጨዋቾች የሚሳተፉበት ክለቦች ሊግ በአገር ውስጥ ሊኖር እንደሚገባ እና ተተኪዎችን ለማፍራት ከ14 ፣ 17 እና ከ20 አመት በታች ተጨዋቾች ላይ መሰራት እንደሚኖርበትም ነው የገለፁት። ዜናው የፋና ነው ዜናው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የሻምበል አበበ ብቂላ ማራቶን ባለፈው እሑድ በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ በወንዶች የፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ለገሰ፣ በሴቶች ደግሞ የመከላከያዋ አፀደ ባይሳ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በ1956 በሮም፣ እንዲሁም በ1960 ዓ.ም. በቶኪዮ በተዘጋጁት የኦሊምፒክ ውድድሮች በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ከአገሩ አልፎ አፍሪካን እንዳኮራ የሚነገርለት ሻምበል አበበ ብቂላ አሁንም ድረስ በስመ ገናናነቱ ይጠቀሳል፡፡ በተለይ ደግሞ በሮም አውራ ጎዳናዎች 42 ኪሎ ሜትር ከ195 ሜትር የሚሸፍነውን ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበበት ታሪኩ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ እየተዘጋጀ ዛሬ ላይ ለደረሰው ዘመናዊ ኦሊምፒክ ተምሳሌት እንደሆነም ይገኛል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያና አትሌቲክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ›› ሆነው እንዲቀጥሉ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ለሚመገርለት ሕያው አትሌት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስሙ የማራቶን ውድድር ማዘጋጀት ከጀመረ ሦስት አሠርታት አስቆጥሯል፡፡ በዚሁ መሠረት ባለፈው እሑድ ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ ባከናወነው ማራቶን በወንዶች ከፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ለገሰ ርቀቱን 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 28 ሰከንድ፣ በሆነ ጊዜ አጠናቆ አንደኛ ሲወጣ፣ ረጋሳ ምንዳዬ ከኦሮሚያ 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 30 ሰከንድ ከፌዴራል ፖሊስ ገዛኸኝ አበራ 2 ሰዓት፣ 13 ደቂቃ፣ 32 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከመከላከያ አፀደ ባይሳ 2 ሰዓት፣ 45 ደቂቃ፣ 60 ሰከንድ፣ እንዲሁም ከዚሁ ክለብ እመቤት ኢተአ 2 ሰዓት፣ 47 ደቂቃ፣ 25 ሰከንድ ስትወጣ፣ በግል የቀረበችው ሻሾ 2 ሰዓት፣ 47 ደቂቃ፣ 26 ሰከንድ ሦስተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡ በቡድን ወንዶች ፌዴራል ፖሊስ፣ በሴቶች ደግሞ መከላከያ አሸናፊ ሆነው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኣሜሪካን ኤምባሲ ባዘጋጀው የጆርናሊዝም ተማሪዎች ውድድር የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሶሰተኛነት ደረጃ ከማግኘቱ በላይ ከኤምባሲው የጆርናሊዝም እና የኮሙኒኬሽን መጽሐፍት ተለግሶለታል።
ዝርዝር ዜናው የኣዲስ ስታንዳርድ ነው፦ The U.S. Embassy in Addis Ababa presented awards to three university students as part of the Embassy’s second Student Journalism Competition. The objective of the competition is to encourage students to gain practical experience in journalism that can be applied to their future careers.A panel of judges, including practicing journalists, reviewed the entries and judged them based on content, presentation, use of resources and research materials. The competition was conducted among university and college students throughout the country. Students submitted stories that were published or broadcast in public or private media outlets. The event was attended by Journalism and Communication Department heads and Community Radio coordinators from eight universities throughout the country. These are the only eight universities with Departments of Journalism and Communication. They participated in a discussion on the nature and importance of community radio. The discussion was moderated by Professor Sam Swan, Director of Internationalization and Outreach at the College of Communication and Information at the School of Journalism and Electronic Media of the University of Tennessee. Etsubedink Hailu from Mekelle University was the first place winner. Endalkachew Abebe from Haramaya University and Feven Abreham from Hawassa University took second and third places respectively. The Public Affairs Section of the Embassy also donated collections of journalism and communication books to each of the eight university representativesinvited to the event. These books will be available at university libraries for all students to access for research and study purposes.Universities that received the donation are: Addis Ababa University, Mekelle University, Bahir Dar University, Hawassa University, Dilla University, Jijiga University, Wollega University, and Madawolabo University. |